የአዲሱ ክልል ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ ስልጣንና ተግባር አዋጅ አጸደቀ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ ስልጣንና ተግባር አዋጅ አጸደቀ፡፡

በምክር ቤቱ ለተነሱ ጉዳዮች በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተጨማሪ ማብራሪያ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

የአስፈጻሚ አካላት መስሪያ ቤቶች የመስተዳድር ምክር ቤት አባል ሆነው በዚህ አዋጅ የተቋቋሙት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

  1. ርዕሰ መስተዳድር
  2. ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር
  3. ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት
  4. ግብርና ቢሮ
  5. ፍትህ ቢሮ
  6. ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
  7. ትምህርት ቢሮ
  8. ጤና ቢሮ
  9. ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ
  10. ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
  11. ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ
  12. ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
  13. የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ
  14. የገቢዎች ቢሮ
  15. ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
  16. ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ
  17. ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
  18. መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
  19. ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ
  20. ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
  21. ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ

ከመስተዳድር ምክር ቤት አባላት ውጭ ያሉት አስፈጻሚ አካላት በዚህ አዋጅ የተቋቋሙ

  1. ግብርና ምርምር ኢንስቲዩት
  2. ቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
  3. ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ
  4. የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  5. መንገድ ባለስልጣን
  6. ከተማ ፕላን ኢንሰቲትዩት
  7. ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
  8. ሚሊሻ ጽ/ቤት
  9. ፖሊስ ኮሚሽን
  10. የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ
  11. ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
  12. የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ
  13. የመሥኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

14.የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ

  1. ጤናና ጤና ነክ አገልግሎትና ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
  2. የህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት