የአገር መከላከያ ሰራዊት በሕዳሴ ግድብ ቀጣና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን ግዳጁን እየተወጣ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የአገር መከላከያ ሰራዊት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጣና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን በጀግንነት ግዳጁን እየተወጣ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ከጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ተሰልፈው ግዳጅ በመፈፀም ላይ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ክልል እና የቤኒንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ አካላትም አገራዊ ተልኳዕቸውን በጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አሻራ ያረፈበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር ግንባታው እተከናወነ ሲሆን ሰራዊቱ በቀጣናው ቀን ከሌት ግዳጁን በማከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጠላት ቀጣናውን ለማተራመስ በቅጥረኛ ተላላኪ ሃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ ትንኮሳ ቢሞክርም በሕዳሴው ዘቦች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሽንፈት መከናነቡን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

በአሁኑ ሰአት በቀጣናው የተሰማሩ የሰራዊታችን ክፍሎች፣ የሜካናይዝድ እና አግረኛ ክፍለጦሮች፣ የክልል የልዩ ኃይል አባላት በተጠንቀቅ ሆነው ግዳጃቸውን በመፈፀም ላይ ይገኛሉም ተብሏል፡፡