ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር ትስስር እንዳላት በተጠረጠረች ግለሰብ ቤት የጦር መሳሪያዎች ተገኙ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር ትስስር እንዳላት በተጠረጠረች ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች ተገኙ።

የአካባቢው ህብረተሰብ ግለሰቧ ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር እንዳላት ባደረሰው ጥቆማ መሰረት በግለሰቧ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከ60 መሰል ጥይቶች ጋር እንዲሁም ሁለት ሽጉጦች ከ20 መሰል ጥይቶች ጋር በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከሽብርተኞቹ ሕወሓትና ሸኔ ጋር የህቡዕ ትስስር በመፈፀም ሀገር በማተራመስና በማፍረስ ሴራው ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ለዋልታ የደረሰው መረጃ አመላክቷል፡፡