የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ለአገር መከላከያ ሰራዊት የ500 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ያስረከቡት የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአገርን ኅልውና ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል።

ማኅበሩ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለቀጣይ ትውልድ እናስረክባለንም ብለዋል።
በዙፋን አምባቸው
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!