ካናዳ ለኢትዮጵያ የ13 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ካናዳ ለኢትዮጵያ የአስቸኳይ ሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት የሚውል የ13 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች፡፡

አገሪቱ በኢትዮጵያ ያለውን የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለማሟላት ነው ተጨማሪ 13 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር ድጋፍ ያደረገችው፡፡

ድጋፉ የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታት አጋር ድርጅቶች ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጓዳኝ የተደረገ መሆኑን የካናዳ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።