ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አመለከቱ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አመልክተዋል፡፡

በተለምዶ ለወንድነት የተሰጠቱት እንደ ጥንካሬ፣ መሪነት፣ ድፍረት፣ ስሜትን መግዛት፣ እርግጠኝነት ወዘተ ያሉ ባህሪያት የሴቶችም ጭምር እንደሆኑ የማወቅን አስፈላጊነት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናግረዋል።

በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማጥፋት ያለመ የመጀመሪያው “የወንዶች ኮንፈረንስ” የአፍሪካ ወንድ መሪዎች በተገኙበት ከኪንሻሳ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አመልክተዋል፡፡

ትናንት በበይነ መረብ በተካሄደው የአፍሪካ ሴት መሪዎች ኔትወርክ የታላላቆች ውይይት ላይ ነው የተካፈሉት ፕሬዝዳንቷ የሠላም ትምህርትን ማስፋፋት ግጭትን ከሥር መሠረቱ ለመከላከል እንደሚያስችል መናገራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡