ሳይፈቀድላቸው የግንባር እንቅስቃሴዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ መንግሥት አሳሰበ

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) የግንባር እንቄስቀሴዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ሆን ብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ጠየቀ፡፡

የግንባር ውሎ መረጃዎችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዕዝ ከተፈቀደለት አካል ውጭ ማሰራጨትን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት ክልከላ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም መንግሥት አሁንም የግንባር መረጃዎችን በተመለከተ በየማኅበራዊ ትስስር ገፆች እያሰራጩ የሚገኙ አካላት መኖራቸውን አሳውቋል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ አገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የአገሪቱን ሕጎች በማክበር በመሆኑ አውቀውም ሆነ ሳያወቁ ይህን ሕግ እየተላለፉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
በትዝታ መንግሥቱ