በቡራዩ ከተማ አሸባሪው ትሕነግን የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግንና አሜሪካን ጨምሮ የአንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራትን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚደግፍ ሰልፍ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ተካሂዷል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን በመሰለፍ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር እንታገላለን ያሉ ሲሆን አሸባሪው ትሕነግና ሸኔ በቅንጅት እየሰሩ ያሉትን ሀገር የማፍረስ ሴራ አጥብቀን እናወግዛለንም ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኖቹ በታሪካችን ጠላቶቻችን ይሆናሉ የሚሉት የሰልፉ ተሳታፊዎች እኛ  ኢትዮጵያውያን ለአጥፊዎቹ ሴራ ሳንበገር ድልን በመጎናፀፍ እናሳፍራቸዋለንም ብለዋል።

በዚህ ሰልፍ ላይም የተለያዩ መፈክሮች የተስተዋሉ ሲሆን እኔም ከመሪዬ ጋር እዘምታለው፣ CNN, BBC, Al Jazeera አሉባልታችሁን አቁሙ፣ Hands Off Afrika፣ #No_more የሚሉት ደግሞ ተጠቃሾቹ ናቸው።

በቡራዩ ከተማ ከተደረገው ሰልፍ ጎን ለጎንም ተሳታፊዎቹ የደም ልገሳና የዓባይ ግድብን ለማፋጠን የቦንድ መግዛት መርኃግብርም ተካሂዷል።

በአሳንቲ ሀሰን