2 የውጭ አገር ዜጎች የገንዘብ ኖትን ለማተም ሲዘጋጁ ተያዙ

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ 2 የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አንድ ካሜሮናዊ እና አንድ ኮቲዲቯራዊ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ ፔንሲዮን ውስጥ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት ፔንሲዮን ውስጥ ነው የኢትዮጵያና የተለያዩ አገራት የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት።
የግለሰቦቹን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ 107 ሺሕ 330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብሮች፣ የተለያዩ አገራት ገንዘቦች፣ ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣ ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ ከተር ወይም የወረቀት መቁረጫ፣ በርካታ ቾክ፣በርካታ ወረቀት፣ 9 ሞባይል ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁሶች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አመልክቷል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!