የኦሮሞ አርቲስቶች የአሸባሪውን ትሕነግ ግብዓተ መሬት ለማፋጠን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለጹ

ኅዳር 21/2014 (ዋልታ) የኦሮሞ አርቲስቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተወያየ ሲሆን የአሸባሪውን ትሕነግ ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ሆነው የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሳኣዳ ኡስማን፣ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አብዱልሀኪም ሙሉ እንዲሁም ታዋቂ የኦሮሞ  አርቲስቶች ተገኝተዋል።

ኅብረተሰቡ የሀገረን ኅልውና ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ስራዊት የበኩሉን ድጋፍ መወጣት እንዳለበትም መልእክት አስተላልፈዋል።

አርቲስቶቹ የ #Nomore ንቅናቄ የተቀላቀሉ ሲሆን በሀገር ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ መልዕከታችውን አስተላልፈዋል።

አረቲስቶቹ ለሀገር ክብር እየተዋደቀ ላለው ጀግናው የሀገር መከላከከያ ሰራዊት የደም ልገሳና ለተፈናቀሉ ዜጎች የአይነት ድጋፍ አድረገዋል።

በእመቤት ንጉሴ