የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ነዋሪዎችና ባለሃብቶች ለመከላከያ ሠራዊት ስንቅ አዘጋጁ

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ህብረተሠቡን በማስተባበር ለመከላከያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅት አድርጓል፡፡

አስተዳደሩ የወረዳውን ነዋሪዎች እና ባለሀብቶችን በማስተባበር 12 ሰንጋ፣ 20 በግ እና ከ7 ሺህ በላይ እንጀራ በማዘጋጀት ወደ ግንባር ለማድረስ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለውና የወረዳውን ነዋሪዎችና ባለሃብቶች በማስተባበር የተዘጋጀው ስንቅ በሰሜን ሸዋ ግንባር ደብረ ብርሃን የሚወሰድ መሆኑም ታውቋል፡፡

በትዝታ ወንድሙ