ከአሸባሪው ቡድን ነፃ በወጡ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ ተጀመረ

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) ከአሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ኃይል ነፃ የወጡ አካባቢዎችን ከስር ከስር እየተከታተለ የጥገናና የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ከተሞች በፍጥነት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስተባብር ቡድን ማቋቋሙን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳወቀ፡፡
በአገልግሎቱ የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ቴክኒካል ሳፖርት ኃላፊ ሺመላሽ ግርማው ከነገ ጀምሮ አንድ ቡድን ወደ ፍላቂት፣ ጋሸናና ጋሸና መስመር ወደሚገኙ ከተሞች የሚንቀሳቀስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን በወልድያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ 13 አገልግሎት መስጫ ማእከላትን እና በደሴ ዲስትሪክት 23 አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን በደብረብርሃን ዲስትሪክቶች ስር የሚገኙ 9 አገልግሎት መስጫ ማእከላት ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉንና እንዲሁም የመሰረተ ልማት ውድመት ማድረሱ ማድረሱ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደምም ወራሪው ቡድን ደቡብ ጎንደር ዞን ገብቶ በነበረበት ወቅት ያወደመውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አካባቢው ነፃ መውጣቱ በመንግስት እንደተገለፀ በተደረገ ርብርብ የመልሶ የማገናኘት ስራ አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ መልሶ እንዲያገኝ መደረጉ መድረጉ ተመላክቷል፡፡
በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና በስራቸው በሚገኙ ሳተላይት ጣቢያዎች ብቻ 2 ሚሊዮን 447 ሺሕ 747 ብር የሚገመት ውድመት መድረሱን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡