ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 28 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ ) ባለፉት አራት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች 1 ነጥብ 28 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለፁት ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 31 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ 1 ነጥብ 28 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ184 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ17 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
የግብርናው ዘርፍ 904 ሚሊዮን ዶላር፣ የማዕድን ዘርፍ 188 ሚሊዮን ዶላር፣ የማምረቻው ዘርፍ 157 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ኤሌክትሪክ 30 ሚሊዮን ዶላር ማስገኘታቸውንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
ቡና 417 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት የመጀመሪያውን ደረጃ ሲይዝ ወርቅ 182 ነጥብ 56 ሚሊዮን ዶላር፣ አበባ 163 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ጫት 148 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል፡፡