የአሌክሳንድሪያ ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ለተፈናቀሉ ወገኖች የ20 ሺሕ ዶላር ድጋፍ አደረጉ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) የአሌክሳንድሪያ ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ከተወሰኑ ምዕመናን ጋር በመሆን የ20 ሺሕ አሜሪካን ዶላር ልገሳ አደረጉ፡፡

ድጋፉንም በሕወሓት ሽብር ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት አገር ቤት ማስተላለፋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

አምባሳደሩ ለቤተ-ክርስቲያኗ እና ለጋሾች መስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡