የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር በ230 ሚሊዮን ብር የሚገነባ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን አስጀመሩ

ሽመልስ አብዲሳ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የወሊሶ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚረዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር እና የውሃ ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት አስጀመሩ።

ፕሮጀክቱ በ230 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን 157 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የወሊሶ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት 7 ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን አሁን የተጀመረው ፕሮጀክት የተመረተውን ውሃ ለተጠቃሚው ለማድረስ የሚረዳ ነው።

የውሃ ማሰራጫ መስመሩ 77 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በሰከንድ 190 ሊትር ያመነጫል ተብሏል።

በአሳየናቸው ክፍሌ (ከወሊሶ)