የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

ኅዳር 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በጉባዔው እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገው ጉባዔው የክልል ኮሚሽነሮች ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በከተሞች የፀጥታ ሁኔታ ማጠናከር ላይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎም ይጠበቃል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።