የቱሪዝም ሚኒስቴር እና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

ኅዳር 25/2014 (ዋልታ) አገርን ከነሙሉ ክብሯ ለማስቀጠል ግንባር ላይ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች ተጠናክረው ቀጥሏል፡፡
በዚህም በዛሬው እለት የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች ግለሰቦች የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለሰራዊቱ አድርገዋል፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ያስረከበ ሲሆን የቱሪዝም ሚኒስቴር በበኩሉ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እና የዓይነት ድጋፍ አስረክቧል፡፡
በቀጣይም አገሪቷን ሰላሟ የማይናጋ መሰረት ላይ ለመትከል ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ከማቋቋም አንስቶ አሸባሪው ሕወሓት ያወደማቸውን ንብረቶች መልሶ በማቋቋም በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቅ ሊሰመርበት ይገባል ተብሏል::
በሔብሮን ዋልታው