ኅዳር 27/2014 (ዋልታ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከ780 በላይ የአክሱም፣ መቀሌና አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀበለ።
ትምህርት ሚኒስቴር የራያ፣ አዲግራት፣ መቀሌ፣ አክሱምና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጊዜያዊ ምደባ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ማዛወሩ ይታወሳል፡፡
የጂማ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች ከዩኒቨርሲቲው ፎረም አባላት በጋራ በመሆን ተማሪዎቹ በሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ከጎናቸው በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹም ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ አሁናዊ ሁኔታ በመነሳት የሰላም አምባሳደርነት ሚና እንዲጫወቱና ከነባር ተማሪዎች ጋር በአብሮነት ስሜት እንዲተባበሩ አመራሮቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለተማሪዎቹ ሲገቡ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ መደረጋቸውንም ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡