በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል እየሰበሰቡ ነው

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ደረጀ ሰማ በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ የሚገኙት በዞኑ የሚገኙ 52 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።

ተማሪዎቹ ተምሮ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚቻለው አገር ሰላም ሲሆን በመሆኑ የአገር ሰላም እስኪረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የዘማች ቤተሰቦች በበኩላቸው ተማሪዎቹ ሰብል በመሰብሰባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።