በጃማይካ የሚኖሩ ‘ራስታፋሪያኖች’ የበቃ ዘመቻ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

ታኅሣሥ 2/2014 (ዋልታ) በጃማይካ የሚኖሩ ‘ራስታፋሪያኖች’ ‘የበቃ #NoMore’ ዘመቻ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

በዘመቻው በኢትዮጵያ ወዳጆች ሰልፍ ሲካሄድ የ’ራስታፋሪያኖች’ የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል።

ትናንት በጃማይካ ኪንግስተን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በተካሄደው ሰልፍ ራስታፋሪያኖቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

‘አሜሪካና አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ ያንሱ፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳዮች በራሷ አቅም መፍታት ትችላለች፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአሸባሪውን ሕወሓት ድርጊት ማውገዝ አለበት’ የሚሉና ሌሎች ተጓዳኝ መልዕክቶችን ሰልፈኞቹ አስተላለፈዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ የተዘጋጀው ‘ራስታፋሪያን’ ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት እንደሆነ ኢዜአ ከበቃ ዘመቻ አስተባባሪዎች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሰልፉ ላይ ከ’ራስታፋሪያኖቹ’ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የአፍሪካ የፀረ-ቅኝ ግዛት ንቅናቄ (ፓን አፍሪካኒዝም) አቀንቃኞችና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል።

‘የበቃ #NoMore’ ዘመቻ ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ወዳጆች ሲካሄድ የ’ራስታፋሪያኖቹ’ የመጀመሪያው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

‘ራስታፋሪያን በጃማይካ በ1930ዎቹ ዓ.ም የተነሳ እንቅስቃሴ፣ እምነትና የአኗርኗር ዘይቤ ነው።