የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

ታኅሣሥ 5/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
አስቸኳይ ጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ፣ የአስተዳደሩን መዋቅራዊ ፕላን ማፅደቂያ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና በማቋቋም ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን በወጡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ከመርኃ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የምክር ቤቱ አባላት አሜሪካንን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራትና መገናኛ ብዙኃኖቻቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና እንዲያቆሙ የተጀመረውን “በቃ” ዘመቻ በግንባር ቀደምነት መቀላቀላቸውን አሳውቀዋል።