ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ አንጎላ አቀኑ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኮትዲቯር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አንጎላ አቀኑ።

ፕሬዝዳንቷ በአንጎላ በሚኖራቸው ቆይታም ከፕሬዘዳንት ጆ ማኑዌል ሎሬንሶ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አንጎላ በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መካከል በአፍሪካ ኅብረት ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እ.ኤ.አ ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣችበት ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና አንጎላ ግንኙነት በተለይም በፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ መስክ ጠንካራ መሆኑ ይነገርለታል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአንጎላ በኋላ ወደ ጋቦን በማቅናት ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል።