አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት በኡጋንዳ የፓን አፍሪካን ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት በኡጋንዳ የፓን አፍሪካን ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ሩጋራማ ዳንኤል (ዶ/ር) ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ሥራ አስፈፃሚው ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ያላቸውን አጋርነት ገልጸው “ኢትዮጵያዊያን በቀኝ ግዛት የነበሩ አፍሪካዊያንን ነጻ ለማውጣት ታግለዋል፤ ዛሬ እኛ ከጎናቸው ለመቆም ባለተራ ነን” ማለታቸውን አምባሳደሯ በቲውተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡