ኬንያዊው ፖለቲከኛ በኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በአካል ባለመገኘቴ ተቆጭቻለሁ አሉ

ታኅሣሥ 10/2014 (ዋልታ) ኬንያዊው ፖለቲከኛ በኮቪድ-19 ተይዤ ከኢትዮጵያ ጎን የምንቆምበት የበቃ ንቅናቄ ላይ በአካል እንዳልገኝ በመሆኔ ቆጭቶኛ ሲሉ ገለፁ፡፡

የኬንያ ብሔራዊ ጉባኤ የቀድሞው ምክትል አፈ ጉባኤ እና የፓርላማ አባል ፋራህ ማሊም ሙሃመድ ትናንት ምሽት ባደረጉት ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ማወቃቸውን በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

በአንድ ዓመት ውስጥ በቫይረሱ ስያዝ ሁለተኛዬ ነው ያሉት ፖለቲከኛው፤ ትልቁ ቁጭቴ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ በሚኖረው የበቃ #Nomore ንቅናቄ ላይ መገኘት አለመቻሌ ነው ብለዋል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ፣ በኢትዮ-ኬንያ የወዳጅነት ማኅበር እና በኬንያ የኤርትራ ኮሚኒቲ አማካኝነት ዛሬ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ8:00 ጀምሮ የ #NOMore ሕዝባዊ መድረክ ይካሄዳል።

ፖለቲከኛው ‹‹አፍሪካ ራሷን ነፃ ማውጣት አለባት›› በማለትም ጸልዩልኝ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡