ንግድ ባንክ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው በነበሩ ቅርንጫፎች አገልገሎት መስጠት ጀመረ

ታኅሣሥ 14/2014 (ዋልታ) በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ቅርንጫፎች አገልገሎት መስጠት ጀምረዋል።

በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ከ30 በላይ ቅርንጫፎች አስፈላጊውን እድሳትና ቁሳቁስ በማሟላት ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ዲስትሪክቱ በዛሬው እለት ተጨማሪ የኤፌሶንና የካራዳሚ ቅርንጫፎችን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡