የገና በዓል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተከበረ ነው

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል (የፈረንጆቹ ገና) በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተከበረ ይገኛል።

የእየሱስ ክርስቶስን ልደት ለማስታወስ በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እያከናወኑ ናቸው።

የካቶሊኩ ጳጳስ ፍራንሲስ በዓሉን ስናከበር የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

አሜሪካ እና አውሮፓን ጨምሮ በርካታ አገራት የገና በዓልን ዛሬ የሚያከብሩ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 አገራት ደግሞ የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ያከብራሉ።