የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ መሆኑ መታወቅ አለበት- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

ታኅሣሥ 18/2019 (ዋልታ) የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ እንደሆነ መታወቅ አለበት ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ100 ቀናት ዕቅድ ትግበራን የገመገመ ሲሆን በመድረኩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ በፕላን ስታቲስቲክስ እና ፖሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ላይ በተካሄደው ግምገማ ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ ምላሽ ሰጥተዋል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር ትልቅ እድልና አማራጭ ገበያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነቶችና ድርድር፣ የገቢ ምርቶች፣ የወጪ ምርቶች፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ተደራሽ ማድረግ፣ 17 ተቋማትን ያካተተ የገበያ ዋጋ ማረጋጋት እና የህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ላይ ጥሩ አፈፃፀም እየታየ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የምርቶቻችን መዳረሻ ማስፋት ይኖርብናል ማለታቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።