አሸባሪው ሕወሓት ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች 11ዱ ስራ ጀመሩ

 
ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 11ዱ ምርት ማምረት መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
አሸባሪ ቡድኑ በደሴና ኮምቦልቻ ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለማቋቋም ሚኒስቴሩ በቦታው ላይ ጊዜያዊ ቢሮ ከፍቶ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን ይታወቃል፡፡
 
ጊዜያዊ ቢሮው ከክልሉ መስተዳድር አካላት፣ ከባለድርሻዎች፣ ከባለሀብቶች እንዲሁም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ባደረገው ቅንጅታዊ ሥራ 11 የጨርቃጨርቅ፣ የምግብና መጠጥ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ምርት የማምረት ሥራ መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡
 
የጊዜያዊ ቢሮው ኃላፊ ጳውሎስ በርጋ እንደገለጹት በአካባቢው የሚገኙ ባንኮች፣ ጉምሩክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤሌክትሪክ ኃይል ሥራ መጀመራቸው ፋብሪካዎቹ ወደ ሥራ እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክቷል፡፡
 
በቅርቡ ኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ሲለቀቅ ተጨማሪ ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንደሚገቡም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!