በትሕነግ ጉዳት ለደረሰበት የጭና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ ተደረገ

ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) ሽብርተኛው የትሕነግ ቡድን ጥቃት ለፈፀመበት የጭና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አንድ አባት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
ቤተ ክርስቲያኑ በጥይት ተበሳስቷል፤ ንዋየ ቅድሳት ተዘርፈዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ ካህናትም በአረመኔው ቡድን በጭካኔ መገደላቸው ይታወሳል።
ነዋሪነታቸው በጭና ቀበሌ የሆኑት ለአሚኮ እንደተናገሩት ምሕረቴ ፈረደ እንደነገሩን አሸባሪው ቡድን ካሕን ልጃቸውን እና የሰባት ዓመት የልጅ ልጃቸውን ፊታቸው ላይ ነው የገደሏቸው፡፡
“ቄስ ነኝ፤ እያላቸውና መስቀል እያሳያቸው ነው የገደሉት” ሲሉ ነው እንባ በዐይናቸው እየወረደ ሁኔታውን ያስታወሱት፡፡
ድጋፉን ያደረጉት ንቡረ ዕድ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ማርቆስ በውጭ የሚኖሩ የነፍስ ልጆቻቸውን በማስተባበር ግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ለጭና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የቆርቆሮ እና ለሕዝቡ የአልባሳት ድጋፍ አስረክበዋል።