የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር 2021 አፍሪካዊያን ዓለም ዐቀፍ ጫናን የመቋቋም ችሎታ እንዳለቸው ያሳዩበት ነው አሉ

ሚኒስትሩ በ2021 መገባደጃ በአፍሪካ ቀንድ ጎልተው የተስተዋሉ ያሏቸውን ሐሳቦች በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በዚህም አንድንድ የውጭ አገራት የራሳቸው ጥቅም ለማስጠበቅ እና ጠባብ ዓላማዎቻቸውን ለማስፈጸም ዓለም ዐቀፍ ሕግጋትን ሲጥሱ ተመልክተናል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ የማነ ዓለምን እያነቃነቀ ባለው የበቃ #NoMore ንቅናቄ የአፍሪካ ቀንድ ሕዝብ ከፍተኛ የሆነ ዓለም ዐቀፍ ጫናን የመቋቋም ችሎታ እንዳለቸው ለዓለም ያስመሰከሩበት ዓመት ነው ሲሉ የአውሮፓዊያኑን 2021 ማጠናቀቂያ ዋዜማ ምክንያት በማድረግ ባሰፈሩት ሐሳብ ገልጸውታል፡፡