የታሪክ ጸሐፊና ተመራማሪው ጄፍ ፒርስ አሸባሪው ትሕነግ የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን መፈፀሙን ገለፀ

ታኅሣሥ 19/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲሰነዝር መክረሙን የታሪክ ጸሐፊ ተመራማሪና የምርመራ ጋዜጠኛው ጄፍ ፒርስ አስታወቀ፡፡

ካናዳዊው የታሪክ ተንታኝ ጄፍ ፒርስ አሸባሪው ያደረሳቸውን ውድመቶች ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

በዚህም ጨጭሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን የትሕነግ የጥፋት ኃይሎች በተደጋጋሚ በመድፍ መመታታቸውን ገልጿል፡፡

ጉዳቱን የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች መልሶ ለመጠገን እንዳስቸገራቸውም ጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ አሸባሪው ቡድን ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ድርጊቱን በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ላይ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ ለቱሪስቶች ማረፊያ የሚሆኑ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶችን አውድሟልም ብሏል፡፡

በተጨማሪም በፖሊስ ጣቢያዎችና በከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአሸባሪው ትሕነግ የጥፋት እጅ አርፎባቸዋል ነው ያለው፡፡

አሸባሪው በደረሰባቸው ቦታዎች ንጹሃንን መግድሉንና ሴቶችና ህጻናትንም መድፈሩንም አስታውሷል፡፡