የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መስጫ አማራጭ ይፋ ሆነ

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ) ኅብረተሰቡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ የሚሰጡበት አማራጮች ይፋ ሆነዋል፡፡
በዚህም ዕጩ ኮሚሽነሮችን
• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988
• በፋክስ ቁጥር 0111233007
• በኢ-ሜል dialoguecommission@gmail.com
• በinfo@hopr.gov.et ወይም
• በአካል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መስፈርቶችም፡-
1/ ዜግነት ኢትዮጵያዊ፣
2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን ማየት
3/ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፣
4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያበረክት የሚችል፣
5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፣
6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፣
7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት፣
8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፣
9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ የሚሉት መሆናቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።