የአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ዛሬ ይመረቃል

የአብርሆት ቤተ መጽሐፍት

ታኅሣሥ 23/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ዛሬ ይመረቃል፡፡

በአዲስ አበባ 4 ኪሎ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው ቤተ መጽሐፍት የማንበብ ባህልን ለማዳበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል።

ቤተ መጽሐፍቱ በዛሬው እለት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚመረቅ ሲሆን በአንድ ጊዜ ከ2 ሺሕ በላይ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችልና በውስጡ ከማንበቢያ ስፍራ በተጨማሪ 8 የመጽሐፍ መሸጫ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ ካፍቴሪያ፣ የህፃናት ማንበቢያ ስፍራዎችን ተካተዋል።

ከዚህ ባለፈም የተለየ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች የሚያነቡበት የመጽሐፍ ክፍል እንዳለው የቤተ መጽሐፍቱ ፕሮጀክት ማናጀር ታሪኩ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ቤተ መፃህፍቱ የተሟላ የመኪና ማቆሚያ እንዳለውም ተገልጿል፡፡