የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ውይይት ተጠናቀቀ

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) “ድል ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል ላለፉት ሦስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ውይይት ተጠናቀቀ፡፡
በውይይቱ የአንድነትና የኅብረ ብሔራዊነት ዘመቻ ድል ባለቤት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል፡፡
የአመራሮቹ ውይይት በኅብረ ብሔራዊ ዘመቻው የተገኙ ድሎች፣ የታዩ ክፍተቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው።
የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ያቀናበሩትን ሴራ በጠንካራ አመራርና የሕዝብ አንድነት ማክሸፍ ተችሏል ነው የተባለው፡፡
ከውይይቱ በኋላ የተፈጠሩ መልካም እድሎችና መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ቆጥሮ በመረከብ ተግባራዊ በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ውይይቱ የጋራ አቀም ላይ የተደረሰበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከነገ ጀምሮ ውይይቱ በክልሉ ዞኖች እና ከተሞች ደረጃ ወርዶ ተመሳሳይ ውይይት እንደሚደሚካሄድ ከኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡