በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ትምህርት መጀመሩ ተገለጸ

ታኅሣሥ 26/2014 (ዋልታ) በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ወረራ ምክንያት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ከሁለት ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ ተጀምሯል።

በሁለቱም ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ መደበኛ ትምህርት የተጀመረ ሲሆን የሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ያሬድ ጌታቸው በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት ሁለት ወር ከ15 ቀን በኋላ በድጋሚ ትምህርት መጀመሩን ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቶቹም ባለው ግብዓት መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስቀጠሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም በትምህርት ቤቶች ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡