ዳያስፖራዎች በአፋር ክልል ለተጎዱ ወገኖች ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

ጥር 6/2014 (ዋልታ) በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች የሚውል የ1 ሚሊዮን 147 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ የኅልውና ዘመቻ በሚል በመላው ስዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተሰበሰበ ነው፡፡
በሌላ በኩል በሶማሊያ አሚሶም የአራተኛ ሴክተር የሰላም አስከባሪ አባላትም ጉዳት በደረሰባቸው በአፋር እና አማራ ክልሎች ድጋፍ የሚውል 1 ሚሊዮን 506 ሺሕ ብር አስረክበዋል።
የሰላም አስከባሪ አባላቱ በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ድጋፉን የተረከቡት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዘሃራ ሁመድ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡