ከተማ ዐቀፍ የሴት አመራሮች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

ከተማ ዐቀፍ የሴት አመራሮች የምክክር መድረክ

ጥር 13/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ድርሻ ለማሳደግ የተዘጋጀ ከተማ ዐቀፍ የሴት አመራሮች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ሴቶች፣ ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ “በሴቶች የአመራር ሰጭነት የበለጸገች ከተማ ለሁሉም” በሚል የተዘጋጀው ፎረም በግራንድ ኤልያናን ሆቴል ነው ኢየተካሄደ የሚገኘው።

የምክክር መድረኩ የሴቶችን የአመራር አቂም ለማጎልበትና የሚገጥማቸውን ችግር በግልጽ ማስረዳት እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ለይ ከወረዳ፣ ክፍለ ከተማ፣ ክልል እና ፌዴራል የሴቶችና ሕፃናት ቢሮዎች  የተውጣጡ አመራሮች ተገኝቷል።

በአሳንቲ ሀሰን