የገንዘብ ሚኒስትሩ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጥር 13/2014 (ዋልታ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያከናወነች ባለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት፣ እድገትንና ልማትን ለማምጣት እንዲሁም ተሳትፎና የሥራ እድሎችን ለማስፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ እንግሊዝ በምትሰጠው ድጋፍ ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በግጭት ሳቢያ በተከሰተው ጉዳት፣ መልሶ በማቋቋም፣ በሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦትና በመሳሰሉት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሁለቱ ሚኒስትሮች በመግባባት መንፈስ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡