ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ ለኢትዮጵያ ተመለሰ

ጥር 13/2014 (ጥር) ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት ላይ የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
ከጎራዴው ጋር ተዘርፎ የነበረው የእንጨት መስቀልም እንዲሁ ተመልሷል።
በተጨማሪም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተላላኳቸው ደብዳቤዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ፖስት ካርዶችና የጽሑፍ እና የምስል ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ቅርሶቹን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስረክቧል።
ቅርሶቹ በታሪክም የሚነገረውን የኢትዮጵያን ቀደምትነትና ሃያልነት በተግባር የሚያሳዩ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ቅርሶቹን ጠብቆና ተንከባክቦ ከማስቀመጥ ባሻገር በቀጣይ የማስተዋወቅ ስራው እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ለፈጣን መረጃዎች፦