ዲያስፖራዎች ህፃናትን ለማሳደግ ቃል የሚገቡበት መርሃግብር ሊካሄድ ነው

ጥር 13/2014 (ዋልታ) ዲያስፖራዎች በችግር ውስጥ የሚገኙ ህፃናትን ለማሳደግ ቃል የሚገቡበት ‘ዲያስፖራ እንደ ወላጅ’ የተሰኘ መርሃግብር ከነገ በስቲያ በብሔራዊ ቤተመንግሥስት ሊካሄድ ነው።

መርሃግብሩ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል።
‘ዲያስፖራ እንደ ወላጅ’ በችግር ውስጥ የሚገኙ ህፃናትን ለማሳደግ ቃል የመግባት ስነ ስርዓት በፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤትና በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር መዘጋጀቱ ተገልጿል።