21ኛው ታላቁ ሩጫ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

               21ኛው ታላቁ ሩጫ

ጥር 15/2014 (ዋልታ) መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው 21ኛው የሩጫ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ዛሬ የተካሄደው የታለቁ ሩጫ ውድድር በሠላም መጠናቀቁ ኢትዮጰያ ሰላም አይደለችም የሚል መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን መረጃቸው ትክክለኛ ያልሆነና ሀሰተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ከመሆኑም ባሻገር ከተማችን አዲስ አበባ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባትና መሰል ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ምቹ መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያ 35ኛውን የአፍሪካ አገራት የመሪዎች ጉባኤ የምታስተናግድ ስለሆነ ኅብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

የመዲናዋ ፖሊስ የዛሬው ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።