በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልል 6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ  

ጥር 16/2014 (ዋልታ) ለላፉት ሦስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ፡፡

በግምገማው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የክልሉን መንግሥት እና የፖለቲካና ግንባታ ሥራዎችን ተንትኖ ጠንካራ ጎኖቹን እና ክፍተቶቹ ለይቷል ነው የተባለው፡፡

በልማትና በፖለቲካው ዘርፍ ባለፉት ሦስት ወራት ሕዝቡን በማሳተፍ በርካታ ስኬታማ ሥራዎች እንደተከናወኑም ተመልክቷል።

በቀጣይም ብልጽግናን ለማረጋገጥ ጠናካራ አመራር እንዲሁም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና የልማት ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ፓርቲው አቅጣጫ ማስቀመጡን ኦቢኤን ዘግቧል።