ሚኒስቴሩ ረቂቅ የፖሊሲ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ ነው

ጥር 19/2014 (ዋልታ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወር ግምገማና ረቂቅ የፖሊሲ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡
በባቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው ግምገማ እንደ ሀገር በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ምን ተሰራ እና በቂ ውሃ ያላቸው ክልሎች ለአጎራባች ክልሎች ተጠቃሚ የሚያደርግበት መንገድ ምን መምሰል አለበት የሚሉ አጀንዳዎች እንደሚዳሰስ ተነግሯል።

የውሃ ሀብትን በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።
ዙፋን አምባቸው (ከባቱ)
ለፈጣን መረጃዎች፦