ኮሚሽኑ በ150 ሚሊየን ብር የተገዙ ተሽከርካሪዎችን ለ5 ክልሎች አስረከበ

                             ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

ጥር 20/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከአውሮፓ ኅብረት በተገኘ 150 ሚሊየን ብር የተገዙ ተሽከርካሪዎችን ለ5 ክልሎች አስረከበ፡፡

ኮሚሽኑ 24 ተሽከርካሪዎች ለ5 ክልሎች የሰጠ ሲሆን 60 ሞተር ሳይክሎችን ለ3 ክልሎች አስረክቧል፡፡

በዚህም ለኦሮሚያ ክልል ሰባት፣ ለአማራ አምስት፣ ለሶማሌ አራት፣ ለደቡብ አራት ፣ ለሲዳማ  ሁለት ተሸከርካሪዎች ተከፋፍሏል፡፡ ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ሥራ አመራር ኮሚሽን ደግሞ 2 ተሰጥቷል፡፡

ከ60ዎቹ ሞተር ሳይክሎች ደግሞ ለሶማሌ 30፣ ለደቡብ 24 እና ለሲዳማ ክልል 6 ተሰጥተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ 4 ዓመት የሚቆይ ሲሆን ሥራ የጀመረው ባለፈው ዓመት መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተስፋዬ አባተ