ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአቡዳቢ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ

ጥር 21/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አቡዳቢ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው “ለእኔና ለልዑካን ቡድኔ ስለ ተደረገልን ደማቅ አቀባበል፣ ለወንድሜ ልዑል ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን ምስጋናዬ ይድረስ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁለቱ ሀገራት ትሥሥር የበለጠ የሚጠናክርበት መንገድ ላይ መክረናል ሲሉም አክለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የልዑካን ቡድን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አቡዳቢ መግባቱ ይታወቃል፡፡