ኢትዮ ቴሌኮም በስድስት ወራት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ጥር 23/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል ብለዋል።

አፈጻጸሙም የእቅዱን 86 ነጥብ 4 በመቶ እንደሆነ መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።