ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የጽናትና አንድነት ተምሳሌት ነው አሉ

ጥር 23/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የጽናት እና አንድነት ተምሳሌት ነው አሉ፡፡

82ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ደማቅ የፈረስ ፌስቲቫል በእንጅባራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ለ82 ዓመታት አባላት አሰባስቦ የቆየው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የጽናት እና አንድነት ተምሳሌት ነው ብለዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው ይሄን ደማቅ በዓል በዩኔስኮ አስመዝግቦ ዓለም ዐቀፍ ቅርስ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

በ1933 ዓ.ም የተመሰረተ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ላለፉት ዓመታት ደማቅ የፈረስ ትዕይንት ሲያሳይ ቆይቷል።

ማኅበሩ ከ59 ሺሕ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን በፌስቲቫሉ ከ3 ሺሕ በላይ ፈረሰኞች ትርኢት አሳይተዋል።