በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እየተሰጠ ነው

ጥር 24/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል አሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና መውሰድ ጀመሩ፡፡
በዚሁ መሠረት በሰሜን ሸዋ ዞን ከ1 ሺሕ 800 በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና መውሰድ መጀመራቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በድሉ ውብሸት ተናግረዋል፡፡
በደሴ ከተማም ፈተናውን 2 ሺሕ 788 ተማሪዎች እየወሰዱ እንደሚገኙና 104 የሚሆኑት የግል ተፈታኞች መሆናቸውን የደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ፍቅር አበበ ለኤፍቢሲ ገልጸዋል።
ፈተናው በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች በጸጥታ ኃይሎች እና በሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡