ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኦሮሚያ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

ጥር 24/2014 (ዋልታ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከወለጋ፣ አምቦ ባኮትቤ ወረዳ እና ከሌሎች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች በአሸባሪው ሸኔ ጥቃት ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ከ6 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ፣ ፍራሽና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃዮች ዩኒቨርሲቲው በምግብና አልባሳት በኩል ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ እንዲያደርግላቸው እና የመልሶ እንዲያቋቁማቸውም መጠየቃቸውን ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡