የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሜዳይ እና የማዕረግ ሽልማት መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ጥር 26/2014 (ዋልታ) የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሜዳይ እና የማዕረግ ሽልማት መርኃግብር በሁመራ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርኃግብሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሠ፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጀነራል ጌታቸው ጉዲናን ጨምሮ የሠራዊቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሠራዊቱ ቤተሠቦች ተገኝተዋል።

በመርኃግብሩ በአውደ ውጊያ ጀብድ የፈፀሙ ምርጥ የሠራዊት አባላት የሜዳይ እና የእውቅና ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

ሽልማቱ አራት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ምርጥ ተዋጊ ክፍሎች፣ ምርጥ አዋጊዎች፣ ምርጥ ተዋጊ እና ምርጥ የስታፍ ሜዳይ ተሸላሚዎች የተካተቱበት መሆኑን አቢሲ ዘግቧል።

የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ ከፍተኛ መኮንኖች እና መስመራዊ መኮንኖች የማዕረግ ማልበስ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል።